የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለውን የመማር ማስተማር ሥራ በቴክኖሎጅ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያለውን የመማር ማስተማር ሥራ በቴክኖሎጅ ለማዘመን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አስታወቀ።

የካቲት 25/2018ዓ.ም ሚዛን አማን:

በኮሌጁ ያለውን የመማር ማስተማር ሥራ በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ውጤታማ የትምህርት አካባቢን ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ገልጿል ።

ኮሌጁ በክልሉ ብቸኛ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲሆን ጥራትና ብቃት ያላቸውን የጤና ባለሙያዎች በስፋት ለማፍራት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ ተናግረዋል ።

ኮሌጁ በአሁኑ ወቅት ከ2ሺህ 414 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ስራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ብቁና ጥራት ያላቸው የጤና ባለሙያዎችን ለማፍራት በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ተማሪዎች በክፍል ከሚወስዱት የንድፈ ሀሳብ ትምህርት ባለፈ በተግባር የተደገፈ እንዲሆን በቂ የቤተሙከራና የልምምድ ጊዜ እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኮሌጁ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ እየሠራ ባለው ሥራ ከክልሉ ጤና ቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ መኖሩንም አቶ ፀጋዬ ተናግረዋል።

ኮሌጁ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ዕውቅና ባገኘባቸው በ3 የትምህርት መስኮች በዲግሪ መርሐግብር 377ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠኑን ገልጸዋል

በተለይ በኮሌጁ የሚማሩ ተማሪዎችን በቂ ዕውቀት ጨብጠው እንዲወጡ ሁለት ዲጂታልና ማንዋል ላይብረሪዎችን ከማዘጋጀት ባለፈ የተግባር ልምምድ የሚያደርጉባቸው በቂ የቤተ ሙከራ ክፍሎች በማደራጀት ትምህርት እየተሰጠ መሆኑን አንስተዋል።

በኮሌጁ ያለውን የትምህርት ስራ በቴክኖሎጅ የተደገፈና እንዲዘምን በማድረግ የመማር ማስተማር ሥራውን ምቹ ለማድረግ በትኩረት እየተሠራ መኾኑንም ጠቅሰዋል።

በተለይ በኮሌጁ ያለው የመማር ማስተማር ስራ ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በመቀናጀት እያደረጉ ያሉት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑንም አቶ ፀጋዬ ጠቁመዋል።

ዘገባው የቤች ሼኮ ቴሌቪዥ ነው።

ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ

‎Website፡ www.mahsc.edu.et

‎Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *