መጋቢት 17/2017 ዓ.ም ሚዛን አማን
ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ሁሉን አቀፍ ለውጥ በሴቶች ተሳትፎ ይረጋገጣል! በሚል መሪ ቃል የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሚዛን ማረሚያ ተቋም ለሚገኙ ሴት ታራሚዎች ስልጠናና ድጋፍ ሰጠ። ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ዲ አቶ ሰብስቤ ኤሊያስ እንዳሉት ኮለጁ ከሚተግብራቸው ተግባራት አንዱ የማህበረስብ አቀፍ አገልግሎት ሲሆን በዚህም ኮሌጃችን የተለያዩ ማሕበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶችን እየከናወነ እንደሚገኝ አስታውሰው የሚዛን ማረሚያ ተቋምም አንዱ የአገልግሎታችን አካል በመሆኑ ይህን ስልጠና መስጠት ማስፈልጉን ተናግረዋል።
ይህ ስልጠና በኮሌጁ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት እና በኮሌጁ ስርዓተ ጾታ ክፍል ጋር በጋራ በመሆን የተዘጋጀ ሲሆን በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ማለትም በማህፀን በር ካንሰር፣ የቤተሰብ ምጣኔ እንዲሁም HIV/AIDSን በተመለከተ በዘርፉ መምህራንና ባለሙያዎች ተሰጥቷል። ስልጠናዉን አስመልክቶ ሃሳባቸዉን ያካፈሉን የተቋሙ ሴት ታራሚዎች እንዳሉት መሰል ስልጠናዎችን መስጠት ከዚህ ቀደም ያለተለመደ መሆኑን አዉስተው በቀጣይም አጠቃላይ የማረሚያ ቢቱን ታራሚዎች ያካተተ አግልግሎት እንዲሰጥ አስተያየታቸዉን ስጥተዋል። የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ላደረገው የሴት ታራሚዎች ስልጠናና ድጋፍ ለተቋማችን አጋዥ ነው ያሉት የሚዛን ማረሚያ ተቋም የማረም እና ማነጽ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ ሳጅን ትግሉ አንቺያብ እንዳሉት ሌሎች ተመሳሳይ ተቋማትም ይህን በጎ ተግባር ልምድ በመውሰድ እገዛ እንዲያደርጉልን ሲሉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምርምር እና ማሕበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን የሆኑት ወ/ሮ መሰረት ገ/ማርያም እንዳሉት የሚዛን ማረሚያ ተቋም ማሕበረሰብ ኮሌጃችን የተለያዩ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን በስፋት ሊሰራባቸው ካቀዳቸው የማህበረሰብ ክፍሎች አንዱ ነው ያሉ ሲሆን ሴቶች ላይ የሚመጣ ለውጥ የማህበረሰብ ለዉጥ በመሆኑ በቀጣይ ለሴት ታራሚዎች የሚደረጉ ዘርፍ ብዙ ድጋፍች ተጠናቀረው ይቀጥላሉ ብለዋል። ወ/ሮ መሰረት አክለውም ለዚህ ፕሮግራም መሳካት ከፍተኛዉን ሚና ለተጫወቱት የማረሚያ ተቋሙ ኃላፊ ሻለቃ ጌትነት በፍቃዱና አጠቃላይ ሰራተኞች ምስጋናቸዉን ያቀረቡ ሲሆን ለስልጠናው ተካፋይ ሴት ታራሚዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቅሶችን በድጋፍ አበርክተዋል።
ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023