04/06/2017 ዓ.ም ሚዛን አማን
የሚዛን አማን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞች ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት የሚዉል ደጋፍ ለማድረግ ያለመ ውይይት አደረጉ። ማክሰኞ 04/06/2017ዓ.ም ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት ድጋፍ ለማድረግ በተዘጋጀው መድረክ ላይ አጠቃላይ የኮሌጁ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ውይይት አድርገዋል። በውይይቱ ላይም የኮሌጁ ዲን አቶ ፀጋዬ አትርሴ እንደተናገሩት የከተማችን ኮሪደር ልማት የሁላችንም ነው በሚል ከተማችንን ዉብ እና ማራኪ ለማድረግ በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ እንደተቋም በኮሌጅ ደረጃ የድርሻችንን ለማበርከት ያለመ መድረክ መሆኑን አስታውሰው ይህን የኮሪደር ልማት ለመደገፍ ሰራተኛዉ ማንም ሳያስገድደው በባለቤትነት ስሜትና በፍቃደኝነት ድጋፍ እንዲያድርግ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በመድረኩ ላይ ሀሳብና አስተያየታቸዉን የሰጡት የኮሌጁ አመራሮች፣ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞች ይህ የኮሪደር ልማት ከተማችንን ዉብ እና ምቹ ለማደረግ ያለመ በመሆኑ በግል ደረጃ በየአካባቢያችን የምናደርገው ድጋፍ እንዳለ ሆኖ እንደተቋም የበኩላችንን መወጣት አለብን በማለት ሀሳባቸዉን አካፍለዋል።
በመጨረሻም ሁሉም የኮሌጁ ሰራተኛ ከየካቲት ወር ደሞዝ የሚቆረጥ የደሞዙን 7% ለሚዛን አማን ከተማ ኮሪደር ልማት ድጋፍ ለማድረግ በሙሉ ድምፅ ወስኗል።
ለወቅታዊ መረጃ ማሕበራዊ ገፆቻችንን ይወዳጁ
Facebook: https://www.facebook.com/fbMACOHS
Telegram: https://t.me/macohs2023